እንኳን ወደ ፒቲሲ የበይነ መረብ ትምህርት ማዕከል በሰላም መጡ፡፡

የፒቲሲ የበይነ መረብ (online) ሥነመለኮት ትምህርት በዲፕሎማ  መርሀ ግብር በአማርኛ ቀርቧል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት ትምህርቱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
2.     በአቀራቢያዎ ወደሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወይንም በሞባይል ባንኪንግ የክፍያ ዘዴ ይፈጽሙ፤

  • የአንድ ኮርስ ዋጋ 150 ብር ነው፤
  • ክፍያ ለመፈጸም የሚከተለውን የትቋማችንን የባንክ ሂሳብ መረጃ ይጠቀሙ፤ 
   • ስም፡ ፔንቴኮስታል ቲዮሎጂካል ኮሌጅ /Pentecostal Theological College
   • የባንክ ሂሳብ ቁጥር፡  1000030114608
   • ባንክ፡ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 
   • ክፍያ ከፈጸሙ በኋላ ባንክ ያስገቡብትን ደርሰኝ/ ስሊፕ በቴሌግራም 0935804541 ፎቶ በማነሳት ይላኩ
3.     በተራ ቁጥር 2 የተዘርዘሩትን መስፈርቶች ከተሟሉ
  •  በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የሚጥናቅቀ ኮርስ ማግኘት ይችላሉ
  •  ኮርሱን በጥንቃቄ ጊዜ ሰጥተው ያንብቡ
  • በንባብ ወቅት መጽሐፍ ቅዱስ እና ማስታወሻ ይያዙ
  • በየክፍለ ትምህርቱ የሚስጡትን የሙከራ ፈተናዎች በግል ይስሩ
  • በኮርሱ መጨርሻ ላይ የማጠቃለያ ፈተና ይሰጣል
  • ፈተናው በአንድ ሰዓት ግዜ ውስጥ ተሰርቶ የሚጠናቀቅ ነው
  • ፈተናውን አንዴ መስራት ከጀመሩ ማቆም አይቻልም፡፡ ስለዚህ ፈተና መስራት ከመጀመሮ በፊት በደንብ ይዘጋጁ
  • የፈተናውን ውጤት ባጠናቅቁበት ሰዓት ወዲያው ያውቃሉ
4.     የዲፕሎማ ፕሮግራሙ 24 ኮርሶችን ይይዛል፡፡ ከፒቲሲ በሥነመለኮት ዲፕሎማ ለመቀበል ሁሉንም ኮርሶች በአጥጋቢ ውጤት ሊያጠናቅቁ ይገባል፡፡


  የሚገኙ ኮርሶች

  “ጸሎት እና አምልኮ” የተባለው ይህ መጽሐፍ፣ ሰው ከሚያስፈልገው እና ከሚፈልገው ነገር ሁሉ የእግዚአብሔርን ክብርና መንግሥት በማስቀደምና ትኩረት በመስጠት ስለሚኖረው የጸሎትና የአምልኮ ሕይወት የሚያስተምር ነው። እንዲህ በማስቀደምና እግዚአብሔርን በማክበር በሚኖረው አማኝ ውስጥ የሚያስፈልገው እንደሚሰጠውም በትኩረት ያስተምራል።

  ትምህርቱ አማኝ የእግዚአብሔር ልጅ የመሆኑን እውነት በመግለጽ ይጀምራል። ልጅ እንደ መሆኑ ጸሎቱ እንደሚሰማ በማመን ወደ አባቱ ዙፋን ይቀርባል። ለኣባቱ ስም፣ መንግሥት እና ፈቃድ በነገር ሁሉ ቅድሚያ ይሰጣል። ይህንን አመለካከት በጸሎቱ ውስጥ ያንጸባርቃል። ከሁሉ በላይ የአባቱን ፈቃድ  ካስቀደመ በኋላ ገና ከመጠየቁ በፊት የሚያስፈልገውን ሁሉ ለሚያውቀው ለእግዚአብሔር የግል ልመናውን ያቀርባል።

  ይህ መጽሐፍ ጸሎት ምን ያህል ከዕለት ኑሮአችን ጋር የተጋመደ እንደሆነ እንድናይ ይረዳናል። በጸሎት ትምህርት ቤት በየትኛውም ደረጃ ላይ ብንሆን ለሕይወታችን የሚያበረክተው አስተዋጽኦ አለው። የትኛውም አማኝና በየትኛወም መስክ ጌታን የሚያገለግል አገልጋይ፣ ይህን መጽሐፍ ቢያጠና ይጠቅመዋል። ይህን መጽሐፍ የሚያጠኑ ሕይወታቸውና አገልግሎታቸው ሁሉ እንዲያድግና በክርስቶስ አካል ውስጥ በቆሙበት ስፍራ ፍሬያማ አገልግሎት እንዲሰጡ ከልብ እንመኛለን።

  ይህንን እና ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶችን በግልም ሆነ በኅብረት ማጥናት የሚፈልጉ ከታች በተሰጠው አድራሻ ሊጽፉልን ይችላሉ። መጽሐፍቱን በንዑስ ቡድን ውስጥ፣ በሥልጠና ፕሮግራሞች ላይ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤቶችም ውስጥ ለመጠቀም ይቻላል።