Phone: 011 552 4395 / 011 552 2331 E-mail: registrar@ptcethiopia.com 

የክርስቲያን ባሕርያት ጥናት (የተትረፈረፈ ሕይወት)

ኮርሱ ክርስቶስን የመምሰል ባሕርያት በአማኝ ሕይወት ውስት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆኑ ለመረዳት ያስችልሃል፡፡በገላ. 5÷22-23 የተዘረዘሩትን ዘጠኙን የመንፈስ ፍሬዎች በሚገባ እንድታውቃቸው፣ በዕለት ሕይወትህ ውስጥ እንድትለማመዳቸውና እንዴት ማፍራት እንደሚቻልም እንድትገነዘብ...

ክርስቲያናዊ መሪነት(የመንፈሳዊ መሪ ተግባርና ግብ)

ይህ ኮርስ መጽሐፍ ቅዱሳዊው አመራር ምን እንደሚመስል በማሳየት ምሳሌ ይሰጠናል፡፡ በራስህም ሆነ በሌሎች ሕይወት ውስጥ ያለውን የመሪነት ሥጦታ እንድትገነዘብና እንድትመዝን ያደርግሃል፡፡ የመሪነትን ክህሎትና አመለካካት አመለካከት እንድታዳብር ከማድረጉም በላይ በዚህ አቅጣጫ ሌሎችን እንድታነሳሳ...

የሕይወት ችግሮችን መፍታት

ይህ ኮርስ በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ የችግር ምንጮች ምን እንደሆኑ ያሳውቅሃል፡፡ ለችግርህም መጽሐፍ ቅዱሳዊ መፍትሔዎችን መጠቀምን ያስተምርሃል፡፡ በመከራና በመንፈሳዊ ዕድገት መካከል ያለውን ግንኙነት ተገነዘባለህ፡፡ በመከራ ውስጥ ያሉ ሰዎችንም እምድታገለግላቸው...

ወንጌል ሥርጭት (የምሥራቹን ቃል ማካፈል)

ላልዳኑ ሰዎች ወንጌል እንዴት እንደምትመሠክርና ወደ ጌታ እንደምትመራቸው በዚህ ኮርስ ውስጥ ትማራለህ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስህን በወንጌል ሥራ ውስጥ እንዴት እንደምትጠቀም በመማር የመንፈስ ቅዱስንም ሥራ እንድታደንቅ ይህ ኮርስ...

የቤተክርስቲያን ተከላ (ራስ ገዝ ቤተ ክርስቲያን)

በዓለም ሁሉ ዙሪያ የኢየሱስ ክርስቶስን ቤተክርስቲያን እንዴት መትከል እንደሚገባ መጽሐፍ ቅዱሳዊውን እቅድ በዚህ ኮርስ ውስጥ ትማራለህ፡፡ በዚህ ውስጥ አንተም እንዴት ድርሻህን እንደምትፈጽም ትገነዘባለህ፡፡ እያንዳንዷ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ሌላ ቤተክርስቲያን እየወለደች መሔዷ የእግዚአብሔር ዕቅድ መሆኑን እንድትረዳና እንድታደንቅ...

የአስተምህሮ መነፈስ ቅዱስ ጥናት (የመንፈስ ቅዱስ ባህሪና አገልግሎት)

መንፈስ ቅዱስ አማካሪ፣ አስተማሪና መሪ እንዲሆነን ጌታ ኢየሱስ ለምን እንደላከው ይህ ኮርስ በስፋት ያስተምራል፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ባሕርያትን በማወቅ ከእርሱ ጋር ግላዊ ግንኙነት የመኖሩን ጥቅም ማስተዋል ትችላለህ፡፡ ኮርሱ የመንፈስ ቅዱስ ሥጦታዎችን በቤተክርስቲያን ውስጥ እንድትፈልጋቸውና መንፈስ ቅዱስ በውስጥህ ፍሬዎችን እንዲያፈራ እንድትፈቅድለት...

የአስተምሮ ደህንነት ጥናት (በክርስቶስ መኖር)

የደህንነት አስተምሮን ዋና ዋና ክፍሎች በዚህ ኮርስ ውስጥ ትገነዘባለህ፡፡ስለ ደኅንነታችን እርግጠኝነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረቱን ትማራለህ፡፡ ኮርሱ በደህንነት ሥራ ውስጥ የእግዚአብሔርን ፍቅር፣ፀጋ፣ጥበብና ኃይል እንድታሰተውልና እንድታደንቅ...

የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ(የእምነታችን መሠረት)

ኮርሱ መሠረታዊ የሆኑትን የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምሮዎች – የሰውን ጅማሬ ፣ ውድቀትና መዋጀት ይይዛል ፡፡ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ግላዊና ዘላለማዊ ግንኙነት ሊኖረው እንደሚፈልግ ትረዳለህ ፡፡ ይህን ኮርስ ስታጠና የመጽሐፍ ቅዱስን ትምህርት እምነትንና ተግባርን በሚመለከት ጉዳይ ሁሉ መለኪያህ እንድታደርገው መሻት ያድርብሃል፡፡ የዓለም ሁሉ ጌታ ሕይወትህንም ይገዛ ዘንድ...
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ዘዴ

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ዘዴ

በዚህ ኮርስ ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትና ጥቅምና ዘዴዎቹን ትገነዘባለህ፡፡ ኮርሱ ተግባራዊ ልምምድ በማድረግ እንዴት እንደምትጠቀምባቸው ለማወቅ ያስችልሃል፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ዕውቀትህንም ለሌሎች ማካፈልን ልምምድህ...
የብሉይ ኪዳን ጥናት(ከዘፍጥረት እስከ ነቢያት)

የብሉይ ኪዳን ጥናት(ከዘፍጥረት እስከ ነቢያት)

በዚህ ኮርስ ዋነኛ ትምህርት የብሉይ ኪዳን መልዕክት ፣የእግዚአብሔር ህዝብ ልምምድና ታሪክ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ህዝብ ስለኖረበት ምድር መሠረታዊ ግንዛቤ ይሰጥሃል፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ላለህ ግንኙነት የሚጠቅሙ እውነቶችን ከብሉይ ኪዳን መጻሕፍት...
የአዲስ ኪዳን ጥናት(የእግዚአብሔር መንግሥት ኃይልና ክብር)

የአዲስ ኪዳን ጥናት(የእግዚአብሔር መንግሥት ኃይልና ክብር)

በዚህ ኮርስ ውስጥ የአዲስ ኪዳንን መልእክትና ታሪካዊ መሠረቱን ትማራለህ፡፡ እግዚአብሔርንም የበለጠ በማወቅ በአዲስ ኪዳን ውስጥ የሚገኙትንም እውነቶች ለሌሎች ለማካፈል ትችላለህ፡፡ በአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ላይ መታመን እንደሚገባም በእርግጠኝነት...
ክርስቲያናዊ ባላደራነት(የእግዚአብሔር ባላደራዎች)

ክርስቲያናዊ ባላደራነት(የእግዚአብሔር ባላደራዎች)

ኮርሱ መሠረታዊ የሆኑትን የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮች – የሰውን ጀማሬ፣ ውድቀትና መዋጀት ይይዛል፡፡ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ግላዊና ዘላላማዊ ግንኙነት ሊኖረው እንደሚፈልግ ትረዳለህ፡፡ ይህን ኮርስ ስታጠና የመጽሐፍ ቅዱስን ትምህርት እምነትና ተግባርን በሚመለከት ጉዳዩ ሁሉ መለኪያህ እንድታደርገው መሻት ያድርብሃል፡፡ የዓለም ሁሉ ጌታ ሕይወትህንም ይገዛ ዘንድ...
መንፈሳዊ ዕድገት

መንፈሳዊ ዕድገት

ይህ ኮርስ ክርስቲያን እንዴት ወደ ብስለት እንደሚደርስ ግንዛቤ ይሰጣል፡፡ በመንፈሳዊ ህይወትህ ለማደግ ምኞት እንዲፈጠርብህ ከማድረጉም በላይ ከእግዚአብሔር ጋር ያለህ ግንኙነት ዘወትር እያደገ እንዲሔድና ይህን ዕድገትህንም በየጊዜው እንድትመዝን...